Micah 6

የእግዚአብሔር ክስ በእስራኤል ላይ

1 እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ፤

“ተነሡ፤ ጕዳያችሁን በተራሮች ፊት አቅርቡ፤
ኰረብቶች እናንተ የምትሉትን ይስሙ፤

2“ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤
እናንት የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፤
ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳል።

3“ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ?
ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው?
እስቲ መልስልኝ!
4ከግብፅ አወጣሁህ፤
ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤
እንዲመሩህ ሙሴን፣
አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።
5ሕዝቤ ሆይ፤
የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣
የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስቲ አስቡ፤
የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣
ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን ዐስቡ።”

6ምን ይዤ በእግዚአብሔር ፊት ልቅረብ፣
በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ?
የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣
ከአንድ ዓመት ጥጃ ጋር ይዤ በፊቱ ልቅረብን?
7በአንድ ሺሕ አውራ በጎች፣
በዐሥር ሺሕ የዘይት ፈሳሽ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልን?
ስለ በደሌ የበኵር ልጄን፣
ስለ ነፍሴም ኀጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብለትን?
8ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤
እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣
በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?

የእስራኤል በደልና ቅጣት

9ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤
ስሙ! እግዚአብሔር ከተማዪቱን እንዲህ እያለ ይጣራል፤
“በትሩን አስቡ፤ ያዘጋጀውም ማን እንደ ሆነ አስታውሱ
የዚህ ስንኝ የዕብራይስጡ ትርጕም በርግጠኝነት አይታወቅም።

10የክፋት ቤት ሆይ፤
በግፍ የተገኘ ሀብታችሁን፣
በሐሰተኛ መስፈሪያ የሰበሰባችሁትን አስጸያፊ ነገር እረሳዋለሁን?
11አባይ ሚዛን የያዘውን ሰው፣
ሐሰተኛ መመዘኛ በከረጢት የቋጠረውን ንጹሕ ላድርገውን?
12ባለጠጎቿ ግፈኞች፣
ሰዎቿ ሐሰተኞች ናቸው፤
ምላሳቸውም አታላይ ናት።
13ስለዚህ አንተን አጠፋሃለሁ፣
ከኀጢአትህ የተነሣ አፈራርስሃለሁ።
14ትበላለህ፤ ነገር ግን አትጠግብም፤
ሆድህ እንዳለ ባዶውን
የዚህ ቃል የዕብራይስጡ ትርጕም በርግጠኝነት አይታወቅም።
ይቀራል፤
ታከማቻለህ፤ ነገር ግን አይጠራቀምልህም፤
የሰበሰብኸውን ለሰይፍ አደርገዋለሁና።
15ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤
የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤
ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም።
16የዖምሪን ሥርዐት፣
የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤
ትውፊታቸውንም ተከትለሃል።
ስለዚህ አንተን ለውድመት፣
ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤
አሕዛብም ይሣለቁብሃል
የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋር ሲስማማ የዕብራይስጡ ግን የሕዝቤን ስድብ ትሸከማለህ ይላል።
።”
Copyright information for AmhNASV